2 ቆሮንቶስ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ካሳዘንኋችሁማ እኔ ካሳዘንሁት በቀር ማን ደስ ያሰኘኛል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ባሳዝናችሁም እንኳ፣ ከእናንተው ካሳዘንኋችሁ በቀር ደስ የሚያሠኘኝ ማን አለ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔስ ባሳዝናችሁ፥ እንግዲያስ በእኔ ምክንያት ከሚያዝን በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም እንኳ እናንተን ባሳዝናችሁ ካሳዘንኳችሁ ከእናንተ በስተቀር እኔን የሚያስደስት ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔስ ባሳዝናችሁ፥ እንግዲያስ በእኔ ምክንያት ከሚያዝን በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን ነው? |
አንዱ የአካል ክፍል ቢታመም ከእርሱ ጋር የአካል ክፍሎች ሁሉ ይታመማሉ፤ አንዱ የአካል ክፍል ደስ ቢለውም የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
እኛ መመኪያችሁ እንደሆን፥ እንዲሁ እናንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን መመኪያችን እንድትሆኑ በከፊል እንዳወቃችሁ ተስፋ እናደርጋለን።
መጀመሪያ በጻፍሁት መልእክት ባሳዝናችሁም እንኳ አያጸጽተኝም፤ ብጸጸትም፥ እነሆ ያች መልእክት ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘነቻችሁ አያለሁ።