እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው።
2 ቆሮንቶስ 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም ብንሆን የተናቅን እንዳይደለን እንደምታውቁ እኔ አምናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ግን ብቁ መሆናችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ግን የማንበቃ እንዳልሆንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ በፈተና አለመውደቃችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ እናደርጋለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ግን የማንበቃ እንዳይደለን ልታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ። |
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው።
ነገር ግን ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ እንደምወደው ሆናችሁ ያላገኘኋችሁ እንደ ሆነ፤ እኔም እንደማትወዱት እሆንባችኋለሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ወይም እኮ በመካከላችሁ ክርክር፥ ኵራት፥ መቀናናት፥ መበሳጨት፥ መዘባበት፥ ወይም መተማማት፥ መታወክ፥ ወይም ልብን ማስታበይ ይኖር ይሆናል።
ስለዚህም እግዚአብሔር ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ በሰጠን ሥልጣን ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እንዳላደርግባችሁ፥ ሥልጣን እንዳለው ሰው ከእናንተ ጋር ሳልኖር ይህን እጽፋለሁ።
በሃይማኖት ጸንታችሁ እንደ ሆነ ራሳችሁን መርምሩ፤ እናንተ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር እንዳለ አታውቁምን? እንዲህ ካልሆነ ግን እናንተ የተናቃችሁ ናችሁ።
ምንም ክፉ ሥራ እንዳትሠሩ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ መልካም ነገር እንድታደርጉ ብቻ ነው እንጂ እኛ ደጎች ልንባል አይደለም፤ እኛም እንደ ተናቁ ሰዎች እንሆናለን።