La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ቆሮንቶስ 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጥን​ቱን አስ​ቀ​ድሜ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም አስ​ቀ​ድሜ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ቀድሞ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ እንደ ነገ​ር​ሁ​አ​ችሁ፥ አስ​ቀ​ድሞ ለበ​ደሉ፥ ለሌ​ሎ​ችም ሁሉ እንደ ገና የመ​ጣሁ እንደ ሆነ ርኅ​ራኄ እን​ዳ​ላ​ደ​ርግ፥ እን​ዲሁ ሳል​ኖር ለሦ​ስ​ተኛ ጊዜ እና​ገ​ራ​ለሁ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሁለተኛው ጕብኝቴ እናንተ ዘንድ በነበርሁበት ጊዜ አስጠንቅቄአችሁ ነበር፤ አሁንም በሩቅ ሆኜ እንደ ገና አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ወደ እናንተም ተመልሼ ስመጣ፣ ከዚህ በፊት ኀጢአት ለሠሩትም ሆነ ለሌሎች አልራራላቸውም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለሁለተኛ ጊዜ ከእናንተ ጋር በነበርሁ ጊዜ እንደነገርኳችሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ እንደገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ለሠሩት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ እናገራለሁ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሁለተኛው ጒብኝቴ ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ በማስጠንቀቅ ተናግሬ ነበር፤ አሁንም ደግሞ በሩቅ ሆኜ ከዚህ ቀደም ኃጢአት ለሠሩትና ለሌሎችም በማስጠንቀቅ እናገራለሁ፤ አሁን ወደ እናንተ ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ለማንም አልራራም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁለተኛ በእናንተ ዘንድ በነበርሁ ጊዜ እንደ ተናገርሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንዲናገር ማስረጃ ከፈለጋችሁ፥ እንደ ገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ላደረጉት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ ብዬአለሁ፥ አስቀድሜም እላለሁ። ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም ነገር ግን በእናንተ ኃይለኛ ነው።

Ver Capítulo



2 ቆሮንቶስ 13:2
8 Referencias Cruzadas  

ሥጋ​ውን ጎድቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን ነፍሱ ትድን ዘንድ እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ለሰ​ይ​ጣን አሳ​ል​ፋ​ችሁ ስጡት።


እኔ ለእ​ና​ንተ በመ​ራ​ራት ወደ ቆሮ​ን​ቶስ እን​ዳ​ል​መ​ጣሁ፥ ስለ ራሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ክር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እነሆ ወደ እና​ንተ ልመጣ ስዘ​ጋጅ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ግን አል​ተ​ፋ​ጠ​ን​ሁም ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን ያይ​ደለ፥ እና​ን​ተን እሻ​ለ​ሁና፤ ልጆች ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸው ያይ​ደለ ወላ​ጆች ለል​ጆ​ቻ​ቸው ሊያ​ከ​ማቹ ይገ​ባ​ልና፤


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ ለማ​ነጽ በሰ​ጠን ሥል​ጣን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ፥ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ሳል​ኖር ይህን እጽ​ፋ​ለሁ።