በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
2 ቆሮንቶስ 12:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ አልከበድሁባችሁም፤ ነገር ግን ምክር ዐዋቂ ሆኜ በመጠበብ ወሰድኋችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሆነው ሆኖ ሸክም አልሆንሁባችሁም፤ ነገር ግን በተንኰልና በዘዴ ያጠመድኋችሁ ሳይመስላችሁ አልቀረም! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁን እንጂ እኔ አልከበድኳችሁም፤ ነገር ግን በብልጠት አታልዬ ያጠመድኳችሁ ሆኖ ተሰምቷችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም ሆነ ይህ ሸክም አልሆንኩባችሁም፤ ለመሆኑ በተንኰልና በማታለል የያዝኳችሁም ይመስላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁን እንጂ እኔ አልከበድሁባችሁም፤ ነገር ግን ሸንጋይ ሆኜ በተንኵኦል ያዝኋችሁ። |
በእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅርታ መመኪያችንና የነፃነታችን ምስክር ይህቺ ናትና፥ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይልቁንም በእናንተ ዘንድ ተመላለስን።
የሚገዙአችሁንና የሚቀሙአችሁን፥ መባያ የሚያደርጓችሁንና የሚታበዩባችሁን፥ ፊታችሁንም በጥፊ የሚመትዋችሁን ትታገሡአቸዋላችሁና።
እከብድባችሁ ዘንድ ወደ እናንተ ካለመምጣቴ በቀር፥ ከአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያሳነስኋችሁ በምንድን ነው? ይህቺን በደሌን ይቅር በሉኝ።
ነገር ግን በስውር የሚሠራውን አሳፋሪ ሥራ እንተወው፤ በተንኰልም አንመላለስ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅል፤ ለሰውም ሁሉ አርአያ ስለ መሆን እውነትን ገልጠን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን እናጽና።
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ታገሡን፥ የበደልነው የለም፤ የገፋነውም የለም፤ ያጠፋነውም የለም፤ የቀማነውም የለም።