2 ቆሮንቶስ 12:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐዋርያት ምልክትስ በፍጹም ትዕግሥትና በተአምራት፥ ድንቅ ሥራ በመሥራትና በኀይላት ተደርጎላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእውነተኛ ሐዋርያ ምልክቶች በመካከላችሁ ተደርገዋል፤ እነርሱም በትዕግሥት መጽናት፣ ምልክቶች፣ ድንቅ ነገሮችና ታምራት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርግጥ የሐዋርያነት ምልክት፥ በምልክትና በድንቅ ነገር፥ በተአምራትም፥ በትዕግሥት በመጽናትም በመካከላችሁ ተከናውኗል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እውነተኛ ሐዋርያ መሆኔን የሚያስረዱት ነገሮች እኔ በመካከላችሁ ሳለሁ በትዕግሥት የፈጸምኳቸው ሥራዎች ናቸው፤ እነዚህም ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ተአምራትም ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርግጥ የሐዋርያነት ምልክት በመካከላችሁ በምልክትና በድንቅ ነገር በተአምራትም በሁሉ ትዕግሥት ተደረገ። |
ወደ እናንተ የመጣና እኛ ወደ አላስተማርናችሁ ወደ ሌላ ኢየሱስ የጠራችሁ ቢኖር፥ ወይም ያልተቀበላችሁት ሌላ መንፈስ ቢኖር፥ ወይም ያልተማራችሁት ሌላ ወንጌል ቢኖር ልትጠብቁን ይገባል።
ነገር ግን በስውር የሚሠራውን አሳፋሪ ሥራ እንተወው፤ በተንኰልም አንመላለስ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅል፤ ለሰውም ሁሉ አርአያ ስለ መሆን እውነትን ገልጠን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን እናጽና።