በነጋ ጊዜም ቀዛፊዎች ቦታውን አልለዩም፤ የሚሄዱበትንም አላወቁም፤ ነገር ግን ለባሕሩ አቅራቢያ የሆነውን የደሴት ተራሮች አዩ፤ መርከባቸውንም ወደ እዚያ ሊያስጠጉ ፈለጉ።
2 ቆሮንቶስ 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምታነቡትንና የምታውቁትን ነው እንጂ፥ ሌላ የምንጽፍላችሁ የለምና፥ ይህንም እስከ ፍጻሜ እንደምታስተውሉት ተስፋ አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልታነብቡት ወይም ልትረዱት የማትችሉትን ነገር አንጽፍላችሁም፤ ሁሉንም እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልታነብቡት ወይም ልትረዱት የማትችሉትን የተለየ ነገር አንጽፍላችሁም፥ ሁሉንም እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንብባችሁ ማስተዋል የምትችሉትን ነገር ካልሆነ ሌላ ምንም አንጽፍላችሁም፤ በሙሉ ማስተዋል እንደምትችሉ ተስፋ አደርጋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምታነቡትና ከምታስተውሉት በቀር ሌላ አንጽፍላችሁምና፤ በጌታችን በኢየሱስ ቀን እናንተ ደግሞ ትምክህታችን እንደምትሆኑ እንዲሁ ትምክህታችሁ እንድንሆን፥ በከፊል ስለ እኛ እንዳስተዋላችሁ ፈጽማችሁ ታስተውሉት ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ። |
በነጋ ጊዜም ቀዛፊዎች ቦታውን አልለዩም፤ የሚሄዱበትንም አላወቁም፤ ነገር ግን ለባሕሩ አቅራቢያ የሆነውን የደሴት ተራሮች አዩ፤ መርከባቸውንም ወደ እዚያ ሊያስጠጉ ፈለጉ።
ነገር ግን በስውር የሚሠራውን አሳፋሪ ሥራ እንተወው፤ በተንኰልም አንመላለስ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅል፤ ለሰውም ሁሉ አርአያ ስለ መሆን እውነትን ገልጠን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን እናጽና።
እግዚአብሔርን መፍራት ዐውቀን ሰዎችን እናሳምናለን፤ ለእግዚአብሔር ግን እኛ የተገለጥን ነን፤ እንዲሁም በልቡናችሁ የተገለጥን እንደ ሆን እንታመናለን።