2 ዜና መዋዕል 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም በመንግሥቱ ከእስራኤል ልጆች ማንንም አገልጋይ አላደረገም፤ እነርሱ ሰልፈኞች፥ የሹሞችም አለቆች፥ የሰረገሎችና የፈረሰኞች ባልደራሶች ነበሩና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ማንንም ባሪያ አላደረገም፤ ይልቁንም እነርሱ ወታደሮቹ፣ ሹማምቱ፣ የጦር አዛዦቹ፣ ሻምበሎቹ፣ የፈረሰኞችና የሠረገለኞች አዛዦቹ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም ለሥራው ከእስራኤል ልጆች ማንንም ባርያ አላደረገም፤ እነርሱ ግን ወታደሮች፥ የሹማምቶችም አለቆች፥ የሰረገሎችና የፈረሰኞች ባልደራሶች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባሪያ አድርጎ አላሠራም፤ እስራኤላውያን ወታደሮች፥ የጦር መኰንኖች፥ የጦር አዛዦች፥ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኀላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ለሥራው ከእስራኤል ልጆች ማንንም ባሪያ አላደረገም፤ እነርሱ ግን ሰልፈኞች፥ የሹማምቶችም አለቆች፥ የሠረገሎችና የፈረሰኞች ባልደራሶች ነበሩ። |
የእስራኤልም ልጆች ያላጠፉአቸውን፥ በኋላቸውም በምድር ላይ የቀሩትን ልጆቻቸውን ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አደረጋቸው።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ አሁንም እኛ የእመቤቲቱ ነን እንጂ የባሪያዪቱ ልጆች አይደለንም፤ ክርስቶስ ነጻ አውጥቶናልና።