ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ሌሊትና ቀን የተገለጡ ይሁኑ።
2 ዜና መዋዕል 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖች ይገለጣሉ፤ ጆሮዎችም ያዳምጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም በዚህ ስፍራ ወደሚጸለየው ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፤ ጆሮዎቼም ያደምጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፥ ጆሮቼም ያደምጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ቤተ መቅደስ እጠብቀዋለሁ፤ በዚህ ቤተ መቅደስ የሚቀርበውንም ጸሎት ሁሉ እሰማለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፤ ጆሮቼም ያደምጣሉ። |
ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ሌሊትና ቀን የተገለጡ ይሁኑ።
ባሪያህ በዚህ ቤት የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ፥ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ቀንና ሌሊት የተገለጡ ይሁኑ።
እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮዎችህ ያድምጡ፤ ዐይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኀጢአት ለአንተ እንናዘዛለን፤ እኔም፥ የአባቴም ቤት በድለናል።
አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይንህን ክፈትና በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ተመልከት።
አምላክህ እግዚአብሔር የሚጐበኛት ሀገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ሁል ጊዜ በእርስዋ ላይ ነው።