Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ባሪ​ያህ በዚህ ቤት የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ፥ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ቀንና ሌሊት የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስምህ እንደሚጠራበት ወደ ተናገርኸው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ዐይኖችህ ሌትና ቀን የተከፈቱ ይሁኑ ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውንም ጸሎት ስማ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ባርያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት እንድትሰማ በዚያ ስሜ ይሆናል ወዳልኸው ስፍራ፥ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ቀንና ሌሊት የተገለጡ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ‘ስሜ ይጠራበታል’ ወዳልከው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቀንና ሌሊት ተመልከት፤ እኔም አገልጋይህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ የምጸልየውን ጸሎት ስማ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ‘በዚያ ስሜ ይሆናል፤’ ወዳልኸው ስፍራ፥ ወደዚህ ቤት ዐይኖችህ ቀንና ሌሊት የተገለጡ ይሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 6:20
17 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ ጆሮ​ህን አዘ​ን​ብ​ልና ስማ፥ አቤቱ፥ ዐይ​ን​ህን ክፈ​ትና እይ፤ በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ የላ​ከ​ውን የሰ​ና​ክ​ሬ​ምን ቃል ስማ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ በእ​ርሱ ዘንድ ፍጹም የሆ​ነ​ውን ያጸና ዘንድ ዐይ​ኖቹ በም​ድር ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታ​ሉና። አሁ​ንም ባለ​ማ​ወ​ቅህ በድ​ለ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ከዛሬ ጀምሮ ጦር​ነት ይሆ​ን​ብ​ሃል።”


እን​ዲ​ህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍ​ርድ ሰይፍ ወይም ቸነ​ፈር ወይም ራብ፥ ቢመ​ጣ​ብን በዚህ ቤት ፊትና በፊ​ትህ እን​ቆ​ማ​ለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመ​ከ​ራ​ች​ንም ወደ አንተ እን​ጮ​ኻ​ለን፥ አን​ተም ሰም​ተህ ታድ​ነ​ና​ለህ።


ነገር ግን አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ ወደ ባሪ​ያህ ጸሎ​ትና ልመና ተመ​ል​ከት፤ ባሪ​ያህ በዚች ዕለት በፊ​ትህ የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎ​ትና ልመ​ና​ውን ስማ።


“አሁ​ንም አም​ላኬ ሆይ፥ በዚህ ስፍራ ወደ​ሚ​ሆ​ነው ጸሎት ዐይ​ኖ​ችህ የተ​ገ​ለጡ፥ ጆሮ​ዎ​ች​ህም የሚ​ያ​ደ​ምጡ ይሁኑ።


እርሱ፦ ሕዝ​ቤን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ በዚያ ለስሜ ቤት ይሠ​ራ​በት ዘንድ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም። በሕ​ዝቤ እስ​ራ​ኤል ላይም ይነ​ግሥ ዘንድ ሰውን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እን​ዲ​ጠ​ራ​ባት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ። በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ ብሎ​አል።


አሁ​ንም በዚህ ስፍራ ለሚ​ጸ​ለይ ጸሎት ዐይ​ኖች ይገ​ለ​ጣሉ፤ ጆሮ​ዎ​ችም ያዳ​ም​ጣሉ።


እኔ ባሪ​ያህ ዛሬ በፊ​ትህ ስለ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሌሊ​ትና ቀን የም​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮ​ዎ​ችህ ያድ​ምጡ፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ይከ​ፈቱ፤ በአ​ንተ ላይም ያደ​ረ​ግ​ነ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ኀጢ​አት ለአ​ንተ እን​ና​ዘ​ዛ​ለን፤ እኔም፥ የአ​ባ​ቴም ቤት በድ​ለ​ናል።


ለመ​ፍ​ረድ ዙፋ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን በዚያ አስ​ቀ​ም​ጠ​ዋ​ልና፥ የዳ​ዊት ቤት ዙፋ​ኖች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በል​ባ​ቸው የዋ​ሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመ​ን​ፈስ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል።


በእኔ ላይ ተሰ​በ​ሰቡ፥ ደስም አላ​ቸው፤ ይገ​ር​ፉኝ ዘንድ ተማ​ከሩ፥ እኔ ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም። ተሰ​በሩ፥ አል​ደ​ነ​ገ​ጡ​ምም።


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከም​ት​ሰ​በ​ስ​በው ፍሬ ሁሉ ቀዳ​ም​ያት ውሰድ፤ በዕ​ን​ቅ​ብም አድ​ር​ገው፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።


በእ​ርሱ ፍጹም መለ​ኮቱ በሥጋ ተገ​ልጦ ይኖ​ራ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos