2 ዜና መዋዕል 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለ፥ “ለአባቴ ለዳዊት በአፉ የተናገረ፥ በእጁም የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እንዲህ አለ፤ “ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ ተናግሮ የሰጠውን ተስፋ፣ እርሱ ራሱ በእጁ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እርሱም እንዲህ ብሎ ነበርና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለ፦ “ለአባቴ ለዳዊት እንዲህ ብሎ በአፉ የተናገረው በእጁም የፈፀመው የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ፤ እርሱም እንዲህ አለው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! እርሱ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠውን የተስፋ ቃል ፈጽሞአል፤ የሰጠውም የተስፋ ቃል እንዲህ የሚል ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አለ “ለአባቴ ለዳዊት በአፉ የተናገረ በእጁም የፈጸመ የእስራኤል እምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤ |
ንጉሡ ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ አባታችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ቡሩክ ነህ።
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፥ “አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ በጕልበታቸውም ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ደግሞም ለንጉሡ።
ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት እንዲህ ብለህ የተናገርኸውን የጠበቅህ፥ በአፍህ ተናገርህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው በእጆችህ ፈጸምኸው።
እርሱ፦ ሕዝቤን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ከእስራኤል ነገድ በዚያ ለስሜ ቤት ይሠራበት ዘንድ ከተማን አልመረጥሁም። በሕዝቤ እስራኤል ላይም ይነግሥ ዘንድ ሰውን አልመረጥሁም።
ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጃቸውን እየዘረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳቸውንም አዘነበሉ፤ በግንባራቸውም ወደ ምድር ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።