ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል በዚህ ስፍራ የሚጸልዩትን ልመና ስማ፤ በተዘጋጀው በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል።
2 ዜና መዋዕል 6:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰው ባልንጀራውን ቢበድል፥ ይምልም ዘንድ በላዩ መሐላ ቢጭንበት፥ እርሱም መጥቶ በዚህ ቤት በመሠዊያህ ፊት ቢናዘዝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢበድልና እንዲምል ቢጠየቅ፣ እርሱም መጥቶ በቤተ መቅደሱ በመሠዊያህ ፊት ቢምል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሰው በባልንጀራው ላይ ኃጢአት ቢሠራ፥ እርሱም መሐላ እንዲምል ቢደረግ፥ እርሱም መጥቶ በዚህ ቤት በመሠዊያህ ፊት ቢምል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ባልንጀራውን መበደሉን የሚገልጥ ክስ ቀርቦበት በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደሚገኘው መሠዊያ አምጥተውት ከበደል ንጹሕ መሆኑን በመሐላ በሚያረጋግጥበት ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ሰው ባልንጀራውን ቢበድል፥ በላዩም መሐላ ቢጫን፥ እርሱም መጥቶ በዚህ ቤት በመሠዊያህ ፊት ቢምል፥ |
ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል በዚህ ስፍራ የሚጸልዩትን ልመና ስማ፤ በተዘጋጀው በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል።
በሰማይ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህም ላይ ዳኛ ሁን፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ መንገዱንም በራሱ ላይ መልስበት፤ ንጹሑንም አጽድቀው፤ እንደ ጽድቁም ክፈለው።
በባልንጀራው ከብት ላይ እጁን እንዳልዘረጋ የእግዚአብሔር መሐላ በሁለታቸው መካከል ይሁን፤ የከብቱም ባለቤት ይህን ከተቀበለ፥ እርሱ ምንም አይክፈል።
“አንድ ሰው ቢበድል፥ የሚያምለውንም ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይናገር በደሉን ይሸከማል፤