La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁ​ንም፥ አቤቱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለባ​ሪ​ያህ ለዳ​ዊት የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል ይጽና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንግዲህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ ለባሪያህ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ፥ አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ! ለባርያህ ለዳዊት የተናገረኸው ቃል ይጽና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንግዲህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአገልጋይህ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ሁሉ እንዲፈጸም አድርግልኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም፥ አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ! ለባሪያህ ለዳዊት የተናገረኸው ቃል ይጽና።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 6:17
10 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ በሰ​ማ​ይም በም​ድ​ርም አን​ተን የሚ​መ​ስል አም​ላክ የለም፤ በፍ​ጹም ልባ​ቸው በፊ​ትህ ለሚ​ሄዱ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ታ​ጸ​ናና የም​ት​ጠ​ብቅ አንተ ነህ።


አሁ​ንም አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆ​ችህ በሕጌ ይሄዱ ዘንድ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ ሰው በፊቴ አይ​ታ​ጣም ብለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት ጠብቅ፤ አጽ​ናም።


“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማ​ያ​ትም ይወ​ስ​ንህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ እን​ግ​ዲ​ያስ እኔ የሠ​ራ​ሁት ይህ ቤት ምን​ድን ነው?


እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቆ​መ​በ​ትን ቦታ አዩ፤ ከእ​ግ​ሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚ​ያ​በራ፥ እንደ ብሩህ ሰን​ፔር ድን​ጋይ የሚ​መ​ስል ወለል ነበረ።


ድሆ​ችና ምስ​ኪ​ኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ምም፤ ምላ​ሳ​ቸ​ውም በጥ​ማት ደር​ቋል፤ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እኔ አል​ተ​ዋ​ቸ​ውም።


በስ​ም​ህም የም​ጠ​ራህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨ​ለማ የነ​በ​ሩ​ትን መዛ​ግ​ብት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የማ​ይ​ታ​የ​ው​ንም የተ​ደ​በ​ቀ​ውን ሀብት እገ​ል​ጥ​ል​ሃ​ለሁ።


ይህም ዛሬ እንደ ሆነ ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ የማ​ል​ሁ​ትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው። እኔም፥ “አቤቱ! ጌታ ሆይ! ይሁን” ብዬ መለ​ስ​ሁ​ለት።


ማኑ​ሄም ተነ​ሥቶ ሚስ​ቱን ተከ​ተለ፤ ወደ ሰው​ዬ​ዉም መጥቶ፥ “ከሚ​ስቴ ጋር የተ​ነ​ጋ​ገ​ርህ አንተ ነህን?” አለው። መል​አ​ኩም፥ “እኔ ነኝ” አለ።