2 ዜና መዋዕል 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ በሰባተኛው ወር በበዓሉ ጊዜ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ተሰበሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ የሰባተኛው ወር በዓል በሚከበርበት ጊዜ፣ በንጉሡ ፊት ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ በሰባተኛው ወር በዓሉን በሚያከብሩ ጊዜ ወደ ንጉሡ ተሰበሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰባተኛው ወር በሚከበረው በዳስ በዓል ጊዜ ሁሉም መጥተው በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ በሰባተኛው ወር በበዓሉ ጊዜ ወደ ንጉሡ ተከማቹ። |
በሰባተኛውም ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በበዓሉ ሰባት ቀኖች፥ የኃጢአቱን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቍርባን ከዘይቱ ጋር እንዲሁ ያቅርብ።”