አንድዋንም ኵሬ፥ በበታችዋም ያሉትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች ሠራ።
ገንዳውና ከሥሩ ያሉትን ዐሥራ ሁለት ኰርማዎች፤
እንዲሁም አንዱንም ኩሬ፥ በበታቹም የሚሆኑትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች አበጀ።
አንዱንም ኵሬ፥ በበታቹም የሚሆኑትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች ሠራ።
ዐሥር መቀመጫዎችንና በመቀመጫዎቹም ላይ መታጠቢያዎችን ሠራ፤
የእግር መታጠቢያዎችን፥ የእጅ መታጠቢያዎችን፥ ጋኖችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜንጦዎችንና ኪራም የሠራውን ሥራ ሁሉ ከንጹሕ ናስ ሠርቶ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት አቀረበለት።