2 ዜና መዋዕል 32:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ ተግዳሮት ጸለዩ፤ ወደ ሰማይም ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ስለዚህ ጕዳይ በጸሎት ወደ ሰማይ ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ ነገር ጸለዩ፥ ወደ ሰማይም ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ፤ እንዲረዳቸውም ወደ እርሱ አጥብቀው ጮኹ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ ጸለዩ፤ ወደ ሰማይም ጮኹ። |
የይሁዳም ሰዎች ወደ ኋላቸው በተመለከቱ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰልፉ በፊታቸውና በኋላቸው ነበረ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከቱን ነፉ።
አሳም፥ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም” ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
እግዚአብሔርም መልአኩን ላከ፤ እርሱም ጽኑዓን ኀያላኑንና መሳፍንቱን አለቆቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወገቡ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።