La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 28:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከኤ​ፍ​ሬም ወገን የነ​በ​ረው ኀያል ሰው ዝክ​ሪም የን​ጉ​ሡን ልጅ ማዓ​ሥ​ያ​ንና የቤ​ቱን አዛዥ ዓዝ​ሪ​ቃ​ምን፥ ለን​ጉ​ሡም በማ​ዕ​ርግ ሁለ​ተኛ የሆ​ነ​ውን ሕል​ቃ​ናን ገደለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጦረኛው ኤፍሬማዊ ዝክሪም የንጉሡን ልጅ መዕሤያን፣ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን ዓዝሪቃምንና ለንጉሡ በማዕርግ ሁለተኛ ሰው የሆነውን ሕልቃናን ገደለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከኤፍሬም ወገን የነበረው ኃያል ሰው ዝክሪ የንጉሡን ልጅ መዕሤያንና የቤቱን አዛዥ ዓዝሪቃምን፥ ለንጉሡም በማዕረግ ሁለተኛ የሆነውን ሕልቃናን ገደለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዚክሪ ተብሎ የሚጠራ አንድ እስራኤላዊ ወታደር የንጉሥ አካዝን ልጅ ማዕሤያን፥ የቤተ መንግሥቱን አስተዳዳሪ ዓዝሪቃምንና በሥልጣን ከንጉሡ ሁለተኛ የሆነውን ሕልቃናን ገደለ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከኤፍሬም ወገን የነበረው ኃይል ሰው ዝክሪ የንጉሡን ልጅ መዕሤያንና የቤቱን አዛዥ ዓዝሪቃምን፥ ለንጉሡም በማዕረግ ሁለተኛ የሆነውን ሕልቃናን ገደለ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 28:7
6 Referencias Cruzadas  

የእ​ር​ሱም በም​ት​ሆን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ሰረ​ገላ አስ​ቀ​መ​ጠው፤ ስገዱ እያ​ለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እን​ዲ​ሄድ አደ​ረገ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው።


ብሩን በአ​ጠ​ፌታ አድ​ር​ጋ​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ውሰዱ፤ በዓ​ይ​በ​ታ​ች​ሁም አፍ የተ​መ​ለ​ሰ​ውን ብር መል​ሳ​ችሁ ውሰዱ፤ ምና​ል​ባት ባለ​ማ​ወቅ ይሆ​ናል።


ሰዎ​ቹም በእ​ጃ​ቸው ያችን እጅ መን​ሻና ብራ​ቸ​ውን በእ​ጥፍ፥ ብን​ያ​ም​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወሰዱ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዮ​ሴ​ፍም ፊት ቆሙ፤ ሰገ​ዱ​ለ​ትም።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ነበ​ርና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ በአ​ንድ ቀን ከይ​ሁዳ ጽኑ​ዓን የነ​በሩ መቶ ሃያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞ​ችን ገደለ፤


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሦስት መቶ ሺህ ሴቶ​ችን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ማረኩ፤ እጅ​ግም ምርኮ ከእ​ነ​ርሱ ወስ​ደው ወደ ሰማ​ርያ አገቡ።