የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም፥ አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡም ቤተ መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።
2 ዜና መዋዕል 24:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑ ኢዮአዳም ከሞተ በኋላ የይሁዳ አለቆች ገብተው ለንጉሡ ሰገዱ፤ ንጉሡም ሰማቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዮዳሄ ሞት በኋላ የይሁዳ ሹማምት መጥተው ለንጉሡ ታማኝነታቸውን ገለጹ፤ ንጉሡም አደመጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮዳሄም ከሞተ በኋላ የይሁዳ አለቆች ገብተው ለንጉሡ እጅ ነሡ፤ በዚያን ጊዜ ንጉሡ ሰማቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮዳሄ ከሞተ በኋላ ግን የይሁዳ መሪዎች ወደ ንጉሥ ኢዮአስ መጥተው እጅ በመንሣት ፍላጎታቸውን ገለጡለት፤ እርሱም በሐሳቡ ተስማማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮዳሄም ከሞተ በኋላ የይሁዳ አለቆች ገብተው ለንጉሡ እጅ ነሡ፤ ንጉሡም እሺ አላቸው። |
የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም፥ አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡም ቤተ መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።
የአባቶቻቸውንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ትተው ባዕድ አምላክንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚያም ወራት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቍጣ ወረደ።
ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ ኀጢአትንም ቢሠራ፥ ኀጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ በአደረገው ዐመፅና በሠራት ኀጢአት በዚያች ይሞታል።
እኔ ዐመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፤ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል፤ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?
እንዲህም ሆነ፤ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ በዓሊምንም ተከትለው አመነዘሩ፤ በዓሊምም አምላክ ይሆናቸው ዘንድ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ።