ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።
2 ዜና መዋዕል 24:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ሰጡ፤ እስኪሞላም ድረስ በሣጥኑ ውስጥ አስገቡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሹማምቱ ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ ግብሩን በደስታ አመጡ፤ እስኪሞላም ድረስ በሣጥኑ ውስጥ ጨመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ደስ ብሎአቸው ግብሩን አመጡ፥ እስኪሞላም ድረስ በሣጥኑ ውስጥ ጣሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሕዝቡንና መሪዎቹን ሁሉ ደስ ስላሰኛቸው ገንዘብ በማምጣት ሣጥኑን ሞሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ደስ ብሎአቸው አቀረቡት፤ እስኪሞላም ድረስ በሣጥኑ ውስጥ ጣሉት። |
ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።
ሣጥኑም በሌዋውያን እጅ ወደ ንጉሡ ሹሞች በደረሰ ጊዜ፥ ብዙ ገንዘብም እንዳለበት ባዩ ጊዜ፥ የንጉሡ ጸሓፊና የሊቀ ካህናቱ ሹም እየመጡ ብሩን ከሣጥን ያወጡ ነበር፤ ሣጥኑንም ደግሞ ወደ ስፍራው ይመልሱት ነበር። እንዲሁም በየቀኑ ያደርጉ ነበር፤ ብዙም ገንዘብ ሰበሰቡ።
የእግዚአብሔርም ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ በእስራኤል ላይ ያዘዘውን ግብር ለእግዚአብሔር ያመጡ ዘንድ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ።
በቸርነትህ የሚታገሡ መንገድህንም የሚያስቡ ይገናኙሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጣህ፤ እኛም ኀጢአት ሠራን፤ ስለዚህም ተሳሳትን።
በብዙ መከራ ከመፈተናቸው የተነሣ ደስታቸው በዝቶአልና፤ በድህነታቸው ጥልቅነትም የለጋስነታቸው ባለጠግነት በዝታለችና።