እነሆ፥ የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከካህናትና ከሌዋውያን ከሦስት አንድ እጅ በመግቢያ በሮች በረኞች ሁኑ፤
2 ዜና መዋዕል 23:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሦስት አንድ እጅም በንጉሡ ቤት ሁኑ፤ ሌላውም ከሦስት አንድ እጅ በመካከለኛው በር ሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሦስተኛው ቤተ መንግሥቱን፣ አንድ ሦስተኛው ‘የመሠረት ቅጽር በር’ የተባለውን ጠብቁ፤ የቀሩት ሰዎች በሙሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሦስቱም አንዱ በንጉሥ ቤት ሁኑ፤ እንዲሁም ከሦስቱ አንዱ በመካከለኛው በር ሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በጌታ ቤት አደባባይ ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላው አንድ ሦስተኛ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ የመጨረሻው አንድ ሦስተኛ እጅ የመሠረት ቅጽር በር ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ ይጠብቅ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ውስጥ ይሰብሰቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሦስት አንድ እጅም በንጉሥ ቤት ሁኑ፤ አንድ እጅም በመካከለኛው በር ሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ይሁኑ። |
እነሆ፥ የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከካህናትና ከሌዋውያን ከሦስት አንድ እጅ በመግቢያ በሮች በረኞች ሁኑ፤
ወደ እግዚአብሔር ቤት ግን ከካህናትና ከሌዋውያን ከሌዋውያኑም አገልጋዮች በቀር ማንም አይግባ፤ እነርሱ ቅዱሳን ናቸውና ይግቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቅ።
ከእናቱ ማኅፀንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተወለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ ሁልጊዜ እየተሸከሙ መልካም በሚልዋት በመቅደስ ደጃፍ ያስቀምጡት ነበር።