La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 22:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አካ​ዝ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ጎቶ​ልያ የተ​ባ​ለች የዘ​ን​በሪ ልጅ ነበ​ረች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አካዝያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ጎቶልያ ትባላለች፤ እርሷም የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው አርባ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ጎቶሊያ የተባለች የዘንበሪ ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አካዝያስ ዕድሜው ኻያ ሁለት ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ገዛ፤ የንጉሥ አክዓብ ልጅ፥ የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ የልጅ ልጅ የሆነች ዐታልያ ተብላ የምትጠራ እናቱ ወደ ክፋት የሚመራ ምክር ትሰጠው ስለ ነበር አካዝያስ የንጉሥ አክዓብን መጥፎ ምሳሌነት ተከተለ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው አርባ ሁለት ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ጎቶሊያ የተባለች የዖምሪ ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 22:2
6 Referencias Cruzadas  

ዘን​በ​ሪም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት፤ ልጁም አክ​አብ በፋ​ን​ታው ነገሠ። 28 ‘ሀ’ ዘን​በ​ሪም ዐሥራ አንድ ዓመት ሲሆ​ነው የአሳ ልጅ ኢዮ​ሳ​ፍጥ ነገሠ። በነ​ገ​ሠም ጊዜ ሠላሳ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ አም​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ጋዙባ የም​ት​ባል የሴ​ላህ ልጅ ነበ​ረች። 28 ‘ለ’ በአ​ባ​ቱም በአሳ መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ጽድ​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ ከእ​ር​ስዋ ፈቀቅ አላ​ለም። በተ​ራ​ሮች የነ​በ​ሩ​ት​ንም አማ​ል​ክት አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም በተ​ራ​ሮቹ ይሠ​ዉ​ላ​ቸ​ውና ያጥ​ኑ​ላ​ቸው ነበረ። 28 ‘ሐ’ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ጋር የሠ​ራው፥ የተ​ዋ​ጋ​ውና ያደ​ረ​ገው ኀይል ሁሉ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው። 28 ‘መ’ በአ​ባ​ቱም በአሳ ዘመን የነ​በ​ረ​ውን ርኵ​ሰት ሁሉ ከም​ድር አስ​ወ​ገደ። በኤ​ዶ​ምም ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም። 28 ‘ሠ’ ንጉሥ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ወር​ቅና ብርን ሊያ​መ​ጡ​ለት ወደ አፌር ይልክ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከብ አሠራ፤ በጋ​ስ​ዮንጋቤር የነ​በ​ረ​ችው መር​ከብ ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም። 28 ‘ረ’ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥን፥ “አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮቼን በመ​ር​ከብ እን​ላክ” አለው። ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እንቢ አለ። 28 ‘ሰ’ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ። በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።


የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ልጅ አግ​ብቶ ነበ​ርና የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።


መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ አካ​ዝ​ያስ የሃያ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አንድ ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ጎቶ​ልያ የተ​ባ​ለች የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዘ​ን​በሪ ልጅ ነበ​ረች።


የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ልጅ አግ​ብቶ ነበ​ርና የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የነ​በ​ሩት ታና​ሹን ልጁን አካ​ዝ​ያ​ስን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት። የመ​ጣ​ባ​ቸው የዓ​ረ​ብና የአ​ሊ​ማ​ዞን የሽ​ፍ​ቶች ጭፍራ የእ​ር​ሱን ታላ​ቆች ወን​ድ​ሞች ገድ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


እና​ቱም ክፉ እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ ትመ​ክ​ረው ነበ​ርና እርሱ ደግሞ በአ​ክ​ዓብ ቤት መን​ገድ ሄደ።