2 ዜና መዋዕል 18:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰረገሎቹም አለቆች የእስራኤል ንጉሥ እንዳልሆነ ባዩ ጊዜ ከእርሱ ተመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሠረገላ አዛዦቹም የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን በተረዱ ጊዜ እርሱን ከማሳደድ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰረገሎቹም አለቆች የእስራኤል ንጉሥ እንዳልሆነ ባዩ ጊዜ እርሱን ከማሳደድ ተመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠረገላዎቹ አዛዦች ኢዮሣፍጥ የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን በተገነዘቡ ጊዜ እርሱን ማሳደድ ተዉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰረገሎቹም አለቆች የእስራኤል ንጉሥ እንዳልሆነ ባዩ ጊዜ እርሱን ከማሳደድ ተመለሱ። |
የሰረገሎችም አለቆች ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእስራኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋጠሙትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፤ እግዚአብሔርም አዳነው፤ አምላኩም ከእርሱ መለሳቸው።
አንድ ሰውም ቀስቱን በድንገት ገትሮ የእስራኤልን ንጉሥ በጥሩሩ መጋጠሚያ በኩል ሳንባውን ወጋው። ሰረገለኛውንም፥ “ተወግቻለሁና እጅህን ግታ፤ ከጦርነት ውስጥ አውጣኝ” አለው።