በከተሞቹ ሁሉ አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦርን አኖረ፤ ከተሞቹንም እጅግ አጠነከራቸው፤ ይሁዳና ብንያምም የእርሱ ወገን ነበሩ።
2 ዜና መዋዕል 17:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ በተመሸጉ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካኖራቸውም ሌላ እነዚህ ንጉሡን ያገለግሉ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ እንግዲህ በመላው ይሁዳ በተመሸጉት ከተሞች ካስቀመጣቸው ሌላ፣ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ በተመሸጉ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካኖራቸውም ሌላ እነዚህ ንጉሡን ያገለግሉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሁሉ ወታደሮች ንጉሥ ኢዮሣፍጥን በኢየሩሳሌም የሚያገለግሉ ሲሆኑ፥ በተጨማሪም ንጉሡ በሌሎቹ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሌሎች ወታደሮችን አስፍሮ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡ በተመሸጉ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካኖራቸውም ሌላ እነዚህ ንጉሡን ያገለግሉ ነበር። |
በከተሞቹ ሁሉ አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦርን አኖረ፤ ከተሞቹንም እጅግ አጠነከራቸው፤ ይሁዳና ብንያምም የእርሱ ወገን ነበሩ።
ብልሃተኛም ሆነ፤ ልጆቹንም ሁሉ በይሁዳና በብንያም ሀገር ሁሉ በምሽጉ ከተሞች ሁሉ ከፋፈላቸው፤ ብዙም ምግብ ሰጣቸው፤ ብዙም ሚስቶች ፈለገላቸው።
በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ሠራዊቱን አኖረ፤ በይሁዳም ሀገር፥ አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች መሳፍንቱን አስቀመጠ።
“ዓለምን ሁሉ የምትገዛ፥ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ፥ የያዕቆብም የጻድቃን ልጆቻቸውም አምላክ ሆይ፥ ሰማይንና ምድርን ከዓለሞቻቸው ጋር የፈጠርህ፥