ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ ቡሩክም ትሆናለህ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፤
2 ዜና መዋዕል 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍጥራቸውም እንደ አባቶቻቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይሁዳ ሻለቆች አለቃው ዓድናስ፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በየቤተ ሰቦቻቸው ሲመዘገቡ እንደሚከተለው ነው፤ ከይሁዳ የየሻለቃው አዛዦች፣ አዛዡ ዓድና ከሦስት መቶ ሺሕ ተዋጊዎች ጋራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጥራቸውም እንደ አባቶቻቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይሁዳ ሻለቆች አለቃው ዓድና፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ ነገድ ለተመለመሉት ወታደሮች አዛዥ ዐድና ተብሎ የሚጠራ የጦር መኰንን ነበር፤ በእርሱም ሥር ሦስት መቶ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጥራቸውም እንደ አባቶቻቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይሁዳ ሻለቆች አለቃው ዓድና፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤ |
ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ ቡሩክም ትሆናለህ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፤
ወደ ሜዳም አወጣውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ከዋክብትን ቍጠራቸው። ዘርህም እንደዚሁ ነው” አለው።
ሮብዓምም ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ እስራኤልን ወግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም ይመልሱ ዘንድ ከይሁዳና ከብንያም ቤት የተመረጡትን አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰልፈኞች ጐልማሶችን ሰበሰበ።
አብያም የተመረጡትን አራት መቶ ሺህ ኀያላን ሰልፈኞች ይዞ ወደ ሰልፍ ወጣ፤ ኢዮርብዓምም የተመረጡትን ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ይዞ በእርሱ ላይ ተሰለፈ።
ለአሳም አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚሸከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሠራዊት፥ ወንጭፍ የሚወነጭፉ፥ ቀስትም የሚገትሩ ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ።
ከእነርሱም ጋር ወደ ሰልፍ የሚወጡ ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሠራዊት ነበሩ፤ እነዚህም ንጉሡን በጠላቱ ላይ የሚያግዙ፥ በታላቅ ኀይል ወደ ሰልፍ የሚወጡ ጽኑዓን ነበሩ።
በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰበሰቡአቸው፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ በየራሱ፥ በየወገኑም፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች፥ በየስማቸው ቍጥር ትውልዳቸውን ተናገሩ።
“የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ ድምር፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በየስማቸው ቍጥር፥ ወንዱን ሁሉ እያንዳንዱን ቍጠሩ።