በዚያም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ተዋረዱ፤ የይሁዳም ልጆች በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ነበርና አሸነፉ።
2 ዜና መዋዕል 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ንጉሥ አሳም ሊጋጠመው ወጣ፤ በመሪሳም ደቡብ አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ተሰለፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሳም ሊገጥመው ወጣ፤ መሪሳ አጠገብ ባለው በጽፋታ ሸለቆም የውጊያ ቦታ ቦታቸውን ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳም ሊጋጠመው ወጣ፥ በመሪሳም አጠገብ ባለው በጽፋታ ሸለቆ ውስጥ ተሰለፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሳም ጦርነት ሊገጥመው ወጣ፤ ሁለቱም ወገኖች ማሬሻ አጠገብ በሚገኘው በጸፋታ ሸለቆ ቦታ ቦታቸውን በመያዝ ለውጊያ ተዘጋጁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳም ሊጋጠመው ወጣ፤ በመሪሳም አጠገብ ባለው በጽፋታ ሸለቆ ውስጥ ተሰለፉ። |
በዚያም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ተዋረዱ፤ የይሁዳም ልጆች በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ነበርና አሸነፉ።
አሳም፥ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም” ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳን የሚዋጋልንም አምላካችን እግዚአብሔር ነው።” ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና።
“ጠላቶችህን ለመውጋት በወጣህ ጊዜ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን ሕዝቡንም ከአንተ ይልቅ በዝተው ባየህ ጊዜ፥ ከግብፅ ሀገር ያወጣህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራቸው።
ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር ሄደ፤ በሴፌት የተቀመጡትንም ከነዓናውያንን መቱ፤ ፈጽመውም አጠፉአት፤ የከተማዪቱንም ስም ሕርም ብለው ጠሩአት።
ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፥ ወደ እነዚህ ቈላፋን ሰፈር እንለፍ፤ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና ምናልባት እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል” አለው።
ዳዊትም ፍልስጥኤማዊዉን አለው፥ “አንተ ሰይፍና ጦር፥ ጋሻም ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።