1 ሳሙኤል 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቈነጃጅቱም፥ “አዎን እነሆ፥ በፊታችሁ ነው። ዛሬ ወደ ከተማዪቱ መጥቶአልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በባማ ኮረብታ ላይ መሥዋዕት ማቅረብ አለባቸውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “አዎን አለ፤ እነሆ፤ ከፊታችሁ ነው፤ ፈጠን በሉ፤ ሕዝቡ በማምለኪያው ኰረብታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ፣ ወደ ከተማችን ገና ዛሬ መምጣቱ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “አዎን አለ፤ እነሆ፤ ከፊታችሁ ነው፤ ፈጠን በሉ፤ ሕዝቡ በማምለኪያው ኰረብታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ፥ ወደ ከተማችን ገና ዛሬ መምጣቱ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጃገረዶቹም “አዎን! እነሆ፥ ሕዝቡ ዛሬ በኮረብታው ላይ መሥዋዕትን ስለሚያቀርብ ባለራእዩ ወደ ከተማይቱ መጥቶአልና ፈጥናችሁ ድረሱበት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ አዎን፥ እነሆ፥ በፊታችሁ ነው፥ ዛሬ ወደ ከተማይቱ መጥቶአልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በኮረብታው ላይ ባለው መስገጃ መሥዋዕት ማቅረብ አለባቸውና ፈጥናችሁ ውጡ። |
ካህኑን ሳዶቅንና ካህናቱን ወንድሞቹን በገባዖን በኮረብታው መስገጃ ባለው በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት አቆማቸው፥
ከዚያም በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ፤ በዚያም ፍልስጥኤማዊው ናሴብ አለ፤ ወደዚያም ወደ ከተማዪቱ በደረስህ ጊዜ በገናና ከበሮ፥ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኰረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያትን ጉባኤ ታገኛለህ።
ሳሙኤልም፥ “እንዴት እሄዳለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል።
የታመነ ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፤ በልቤም፥ በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፤ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።
አባትህም ቢፈልገኝ፦ ለዘመዶቹ ሁሉ በዚያ በቤተ ልሔም የዓመት መሥዋዕት አላቸውና ዳዊት ወደ ከተማው ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ አጽንቶ ለምኖኛል በለው።
ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፤ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።