ሕዝቅያስም ደብዳቤውን ከመልእክተኞች እጅ ተቀብሎ አነበበው፤ ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው።
1 ሳሙኤል 8:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም የሕዝቡን ቃል ሁሉ ሰማ፤ ለእግዚአብሔርም ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ሕዝቡ ያለውን ሁሉ ሰማ፤ ያንኑ በእግዚአብሔር ፊት ተናገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ሕዝቡ ያለውን ሁሉ ሰማ፤ ያንኑ ለጌታ ተናገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም እነርሱ ያሉትን ሁሉ አዳመጠ፤ ከዚያም ሄዶ ለእግዚአብሔር ነገረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም የሕዝቡን ቃል ሁሉ ሰማ፥ ለእግዚአብሔርም ተናገረ። |
ሕዝቅያስም ደብዳቤውን ከመልእክተኞች እጅ ተቀብሎ አነበበው፤ ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው።
ዮፍታሔም ከገለዓድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም መስፍን ይሆናቸው ዘንድ በላያቸው አለቃ አድርገው ሾሙት፤ ዮፍታሔም ቃሉን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በመሴፋ ተናገረ።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “ቃላቸውን ስማ፤ ንጉሥም አንግሥላቸው” አለው። ሳሙኤልም የእስራኤልን ሰዎች፥ “እያንዳንዳችሁ ወደ ከተማችሁ ሂዱ” አላቸው።