ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፤ አዋረዳቸውም፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ጌትንና መንደሮችዋን ወሰደ።
1 ሳሙኤል 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ከአስቀሎና ጀምሮ እስከ፤ ጌት ድረስ ከእስራኤል ልጆች የወሰዱአቸው ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱ፤ እስራኤልም ድንበሩን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወሰዱ። በእስራኤልና በአሞራውያን መካከልም ሰላም ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከአቃሮን እስከ ጋት የነበሩ ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱላት፤ ግዛታቸውም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ነፃ ወጣች፤ በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ሰላም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከዔቅሮን እስከ ጌት የነበሩ ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱላት፤ ግዛታቸውም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ነፃ ወጣች፤ በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ሰላም ወርዶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን የያዙአቸው በዔቅሮንና በጋት መካከል የነበሩትም ከተሞች ሁሉ ለእስራኤላውያን ተመለሱላቸው፤ እስራኤላውያንም ድንበሮቻቸውን ከፍልስጥኤማውያን እጅ አዳኑ፤ በእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከልም ዕርቀ ሰላም ወርዶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም ከአስቀሎና ጀምሮ እስከ ጌት ድረስ ከእስራኤል የወሰዱአቸው ከተሞች ለእስራኤል ተመለሱ፥ እስራኤልም ድንበሩን ከፍልስጥኤማውያን እጅ አዳነ። በእስራኤልና በአሞራውያንም መካከል ዕርቅ ነበረ። |
ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፤ አዋረዳቸውም፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ጌትንና መንደሮችዋን ወሰደ።
ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዘሮች አየን፤ በአዜብ በኩል ዐማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮችዋም ኬጤዎናዊውና ኤዌዎናዊውም፥ ኢያቡሴዎናዊው፥ አሞሬዎናዊውም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊውም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ተቀምጦአል።”
አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የአሕዛብ ምርኮ ትበላለህ፤ ዐይንህም አታዝንላቸውም፤ ያም ለአንተ ክፉ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በመታሃቸው ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፤ አትማራቸውም፤
አምስቱም የኢያቡሴዎን ነገሥት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የላኪስ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፤ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።
ድንበሩም ወደ አቃሮን ደቡብ ይወጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመለሳል፤ ድንበሩ ወደ ሰቆት ይወጣል፤ ወደ ደቡብም ያልፋል፤ በሌብና በኩልም ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
ሲሣራም ወደ ጓደኛው ወደ ቄናዊው ወደ ሔቤር ሚስት ወደ ኢያዔል ድንኳን በእግሩ ሸሸ፤ በአሶር ንጉሥ በኢያቢንና በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ነበርና።