1 ሳሙኤል 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “ስለ መቅሠፍቱ የምንሰጠው የበደል መባእ ምንድን ነው?” አሉ። እነርሱም እንዲህ አሉ፥ “እናንተንና አለቆቻችሁን፥ ሕዝባችሁንም ያገኘች መቅሠፍት አንዲት ናትና እንደ ፍልስጥኤማውያን አለቆች ቍጥር አምስት የወርቅ እባጮች፥ አምስትም የወርቅ አይጦች አቅርቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያንም፣ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዐይነት በመሆኑ፣ በፍልስጥኤማውያን ገዦች ቍጥር ልክ ዐምስት የወርቅ ዕባጮችና ዐምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዓይነት በመሆኑ፥ በፍልስጥኤማውያን ገዥዎች ቍጥር አምስት የወርቅ ዕባጮችና አምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም፥ “ስለ በደል የሚከፈል ይሆን ዘንድ ከምን ዐይነት ስጦታ ጋር እንላከው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “በእባጩ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጒልቻ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ብዛት በአይጥ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጉልቻ መሆን አለበት፤ በእናንተ ሁሉና በአምስቱ ገዢዎች ላይ የተላከው መቅሠፍት አንድ ዐይነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ ስለ በደል መሥዋዕት የምንመልስለት ምንድር ነው? አሉ። እነርሱም እንዲህ አሉ፦ እናንተንና አለቆቻችሁን ያገኘች መቅሠፍት አንዲት ናትና እንደ ፍልስጥኤማውያን አለቆች ቁጥር አምስት የወርቅ እባጮች አምስትም የወርቅ አይጦች አቅርቡ። |
በግብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአምስቱ የፍልስጥኤም ግዛቶች ለጋዛ፥ ለአዛጦን፥ ለአስቀሎና፥ ለጌት፥ ለአቃሮን፥ እንዲሁም ለኤዌዎናውያን በተቈጠረችው በከነዓን ግራ በኩል እስካለችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤
የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስቀሎናም ወረደ፤ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፍፎ እንቆቅልሹን ለነገሩት ሰዎች ሰጠ። ሶምሶንም ተቈጣ፤ ወደ አባቱም ቤት ተመለሰ።
እነርሱም አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥ ከነዓናውያንም ሁሉ ፥ ሲዶናውያንም፥ ከበዓልሄርሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራ የሚኖሩትም ኤዌዎናውያን፤
የእግዚአብሔር ታቦት ወደዚያ በገባች ጊዜ በከተማው ሁሉ ታላቅ ሁከት ሆኖአልና። በሕይወትም ያሉ፥ ያልሞቱትም ሰዎች በእባጭ ተመቱ፤ የከተማዪቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ።
የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፤ ክፉም ነገር አመጣችባቸው፤ በእነርሱም ላይ በመርከቦች ውስጥ ወጣ፤ የአዛጦንንና የአውራጃዎችዋንም ሰዎች የውስጥ አካላቸውን በዕባጭ መታ፤ በከተሞቻቸውም መካከል አይጦች ወጡ፤ በከተማውም ታላቅ መቅሠፍት ሆነ።
ከሄደችም በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከትም ሆነ፤ የከተማዪቱንም ሰዎች ታላቁንም ታናሹንም መታ፤ የውስጥ አካላቸውንም በእባጭ መታቸው፤ የጌት ሰዎችም የውስጥ አካላቸውን ምስል ሠሩ፥
እጁ ከእናንተና ከአማልክቶቻችሁ፥ ከምድራችሁም ይቀልል ዘንድ፥ የእባጫችሁን ምሳሌ፥ ምድራችሁንም የሚያጠፉትን የአይጦችን ምሳሌ አድርጋችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብርን ስጡ።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስዳችሁ በሰረገላው ላይ አኑሩአት፤ ስለበደል መባእ ካሳ አድርጋችሁ ያቀረባችሁትን የወርቁንም ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቷ አጠገብ አኑሩት፤ ትሄድም ዘንድ ስደዱአት።