የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሰረገላ ላይ ጫኑአት፥ በኮረብታውም ላይ ከነበረው ከአሚናዳብ ቤት አመጡአት፤ የአሚናዳብ ልጆችም ዖዛና ወንድሞቹ ታቦቷ ያለችበትን ሰረገላ ይነዱ ነበር።
1 ሳሙኤል 6:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ የወርቁ አይጦችና የአካላቸው እባጮች ምሳሌ ያሉበትንም ሣጥን በሰረገላው ላይ ጫኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርንም ታቦት፣ የወርቁን ዐይጦችና የዕባጮቹን ምስሎች በሠረገላው ላይ ጫኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ታቦት በአይጦችና በእባጮች ምስል ከተሠራ ወርቅ ከተሞላበት ሣጥን ጋር በሠረገላው ላይ አስቀመጡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስደው በአይጦችና በእባጮች አምሳል የተሠራ ወርቅ ከተሞላበት ሣጥን ጋር በሠረገላው ላይ አስቀመጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ የወርቁ አይጦችና የእባጮቻቸው ምሳሌ ያሉበትንም ሣጥን በሰረገላው ላይ ጫኑ። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሰረገላ ላይ ጫኑአት፥ በኮረብታውም ላይ ከነበረው ከአሚናዳብ ቤት አመጡአት፤ የአሚናዳብ ልጆችም ዖዛና ወንድሞቹ ታቦቷ ያለችበትን ሰረገላ ይነዱ ነበር።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በተገኘ በአዲስ ሰረገላ ላይ አኖሩአት። ዖዛና ወንድሞቹም ሰረገላውን ይነዱ ነበር።
ፍልስጥኤማውያንም እንዲሁ አደረጉ፤ የሚያጠቡትን ሁለቱን ላሞች ወሰዱ፤ በሰረገላውም ጠመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ዘጉባቸው፤
ላሞችም ወደ ቤትሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ አቅንተው “እምቧ” እያሉ በጎዳናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላሉም፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆችም እስከ ቤትሳሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር።
እነርሱም፥ “ስለ መቅሠፍቱ የምንሰጠው የበደል መባእ ምንድን ነው?” አሉ። እነርሱም እንዲህ አሉ፥ “እናንተንና አለቆቻችሁን፥ ሕዝባችሁንም ያገኘች መቅሠፍት አንዲት ናትና እንደ ፍልስጥኤማውያን አለቆች ቍጥር አምስት የወርቅ እባጮች፥ አምስትም የወርቅ አይጦች አቅርቡ።