እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፤ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ፤ ሰዎችም በአንድ ወይም በሁለት ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደ ሆነ ከብቶቹ ሁሉ ይሞታሉ።
1 ሳሙኤል 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም እንዲሁ አደረጉ፤ የሚያጠቡትን ሁለቱን ላሞች ወሰዱ፤ በሰረገላውም ጠመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ዘጉባቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንደ ተነገራቸው አደረጉ፤ ሁለት ላሞች ወስደው ሠረገላ በታሰረበት ቀንበር ጠመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሰው ዘጉባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎቹም እንዲሁ አደረጉ፥ የሚያጠቡትን ሁለቱን ላሞች ወሰዱ፥ በሰረገላም ጠመዱአቸው፥ እንቦሳቻቸውንም በቤት ዘጉባቸው፥ |
እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፤ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ፤ ሰዎችም በአንድ ወይም በሁለት ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደ ሆነ ከብቶቹ ሁሉ ይሞታሉ።
በሰባተኛውም ጊዜ፥ “እነሆ፥ የሰው ጫማ የምታህል ትንሽ ደመና ከባሕር ውኃ ቋጥራ ስትወጣ አየሁ” አለ። እርሱም፥ “ወጥተህ አክዓብን፦ ዝናብ እንዳይዝህ ሰረገላህን ጭነህ ውረድ በለው” አለ።
የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ የወርቁ አይጦችና የአካላቸው እባጮች ምሳሌ ያሉበትንም ሣጥን በሰረገላው ላይ ጫኑ።
ወደምትሄድበትም ተመልከቱ፤ በድንበሩም መንገድ ላይ ወደ ቤትሳሚስ ብትወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እርሱ ነው፤ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን።”