1 ሳሙኤል 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱአት፤ ከአቤኔዜርም ወደ አዛጦን ይዘዋት መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት ከማረኩ በኋላ፣ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ ወሰዱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ከማረኩ በኋላ፥ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ ወሰዱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከማረኩ በኋላ ከአቤንዔዜር አሽዶድ ተብላ ወደምትጠራ ከተማቸው ወሰዱአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ፥ ከአቤንኤዘርም ወደ አዛጦን ይዘውት መጡ። |
በፋርስ ሀገሮችና በግብፅ ሀገሮች ዐውጁና፥ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጥዋም የሆነውን ታላቁን ተአምር፥ በመካካልዋም ያለውን ግፍ ተመልከቱ” በሉ።
ፊልጶስም አዛጦን ወደምትባል ሀገር ደረሰ፤ በከተማዎችም ሁሉ እየተዘዋወረ ወደ ቂሳርያ እስኪደርስ ድረስ ያስተምር ነበር።
በግብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአምስቱ የፍልስጥኤም ግዛቶች ለጋዛ፥ ለአዛጦን፥ ለአስቀሎና፥ ለጌት፥ ለአቃሮን፥ እንዲሁም ለኤዌዎናውያን በተቈጠረችው በከነዓን ግራ በኩል እስካለችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤
በእነዚያም ወራት እንዲህ ሆነ። ፍልስጥኤማውያን ለጦርነት በእስራኤላውያን ላይ ተሰበሰቡ። እስራኤልም ሊዋጉአቸው ወጡ፤ በአቤኔዜር አጠገብም ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም በአፌቅ ሰፈሩ።
ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በመሴፋና በአሮጌው ከተማ መካከል አኖረው፤ ስሙንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድኤት ማለት ነው።