በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል።
1 ሳሙኤል 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መብራት ገና አልጠፋም ነበር፤ ሳሙኤልም የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር መቅደስ ተኝቶ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ደግሞ የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ የእግዚአብሔር መብራትም ገና አልጠፋም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር መብራትም ገና አልጠፋም ነበር፤ ሳሙኤል ደግሞ የጌታ ታቦት ባለበት፥ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገና የቤተ መቅደሱ መብራት ሳይጠፋ ሳሙኤል የተቀደሰው የቃል ኪዳን ታቦት ባለበት መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም በስፍራው ተኝቶ ሳለ፥ የእግዚአብሔርም መብራት ገና ሳይጠፋ፥ ሳሙኤልም የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር መቅደስ ተኝቶ ሳለ፥ |
በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል።
“መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ የመቅረዙም እግሩና ቅርንጫፎቹ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ ጽዋዎቹም፥ ጕብጕቦቹም፥ አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።
እንደ መከራዋና እንደ ኀዘንዋም እግዚአብሔር ልጅ አልሰጣትም ነበር። ስለዚህም ታዝን ነበር። እግዚአብሔር ማኅፀንዋን ዘግትዋልና፥ ልጆችንም አልሰጣትምና።
በሴሎም ከበሉ በኋላ ሐና ተነሣች። በሴሎም በእግዚአብሔር ፊት ቆመች። ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ መቃን አጠገብ በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር።