1 ሳሙኤል 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሊም ሳሙኤልን ጠርቶ፥ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሊ ግን ሳሙኤልን፣ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም፣ “እነሆኝ” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሊ ግን ሳሙኤልን፥ “ልጄ ሳሙኤል ሆይ” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም፥ “እነሆኝ” ሲል መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሊ ግን ሳሙኤልን “ልጄ ሳሙኤል ሆይ!” ሲል ጠራው። ሳሙኤልም “እነሆ አለሁ ጌታዬ!” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም ሳሙኤልን ጠርቶ፦ ልጄ ሳሙኤል ሆይ፥ አለ፥ እርሱም፦ እነሆኝ አለ። |
እስራኤልም ዮሴፍን፥ “ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን የሚጠብቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እልክህ ዘንድ ና” አለው። እርሱም፥ “እሺ” አለው።
አሁንም እነሆ፥ ንጉሡ በፊታችሁ ይሄዳል፤ እኔም አርጅቻለሁ፤ እንግዲህም አርፋለሁ፤ እነሆም፥ ልጆቼ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔም ከሕፃንነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊታችሁ ሄድሁ።
እርሱም፥ “እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድን ነው? ከእኔ አትሸሽግ፤ ከነገረህና ከሰማኸው ነገር ሁሉ የሸሸግኸኝ እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብህ፤ እንዲህም ይጨምርብህ” አለው።