1 ሳሙኤል 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን በቤቱ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ በዔሊ ላይ አጸናለሁ፤ እኔም ጀምሬ እፈጽምበታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተ ሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ አስቀድሜ የተናገርኩትን ብርቱ የማስጠንቀቂያ ቃል ሁሉ በተግባር እፈጽማለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን በቤቱ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ በዔሊ አወርዳለሁ፥ እኔም ጀምሬ እፈጽምበታለሁ። |
ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።
እግዚአብሔር እንደ ሰው የሚታለል አይደለም። እንደ ሰው ልጅም የሚዛትበት አይደለም፤ እርሱ ያለውን አያደርገውምን? አይናገረውምን? አይፈጽመውምን?
አምላካችሁ እግዚአብሔር የተናገረው መልካም ነገር ሁሉ እንደ ደረሰላችሁ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እናንተን እስኪያጠፋችሁ ድረስ እግዚአብሔር እንዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመጣባችኋል።
የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢንንም እስኪያጠፉ ድረስ በከነዓን ንጉሥ በኢያቢን ላይ የእስራኤል ልጆች እጅ እየበረታች ሄደች።
ያም ሰው መልሶ፥ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ደግሞም በሕዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖአል፥ ሁለቱም ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም ታቦት ተማርካለች” አለው።
እርስዋም የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከች፥ ስለ አማቷና ስለ ባልዋም፦ የሕፃኑን ስም ዊቦርኮኢቦት ብላ ጠራችው።