1 ሳሙኤል 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናው ሳሙኤልም በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይታይም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ ጌታን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የጌታ ቃል ዘወትር የሚሰማ አልነበረም፤ ራእይም አይታይም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወጣቱ ሳሙኤል በዔሊ የአመራር ሥልጣን ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር አይሰማም ነበር፤ ራእይም አይታይም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናውም ሳሙኤል በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፥ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፥ ራእይም አይገለጥም ነበር። |
ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፤ ወዮታ በወዮታ ላይ ይከተላል፤ ከነቢዩም ዘንድ ራእይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ሕግ፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል።
በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተዉት። እነርሱም ወደ አርማቴም ወደ ቤታቸው ገቡ፤ ልጁም በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
የታመነ ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፤ በልቤም፥ በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፤ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።
ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፤ ከካህናትም ወደ አንዲቱ ዕጣ፥ እንጀራ ወደምበላበት እባክህ ላከኝ ብሎ ለአንድ ብር መሐልቅ ለቍራሽ እንጀራ በፊቱ ይሰግዳል።”
እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ። እግዚአብሔር ለሳሙኤል ይገለጥለት ነበርና። ሳሙኤልም ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ በእስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደ ሆነ ታመነ። ዔሊም እጅግ አረጀ፥ ልጆቹ ግን በክፋት ጸንተው ኖሩ፤ መንገዳቸውም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር።