ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፤ ልትሸሽም ስትሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፌቡስቴ ነበረ።
1 ሳሙኤል 29:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትና ሰዎቹም ማልደው ይሄዱ ዘንድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ሀገር ይመለሱ ዘንድ ተነሡ። ፍልስጥኤማውያንም ሊዋጉ ወደ ኢይዝራኤል ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ለመመለስ በማለዳ ተነሡ፤ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ኢይዝራኤል ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ለመመለስ በማለዳ ተነሡ፤ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ኢይዝራኤል ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊትና ተከታዮቹ በማግስቱ ማለዳ ወደ ፍልስጥኤም ተመልሰው ለመሄድ ተነሡ፤ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ኢይዝራኤል ዘመቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትና ሰዎቹም ማልደው ይሄዱ ዘንድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም አገር ይመለሱ ዘንድ ተነሡ። ፍልስጥኤማውያንም ወደ ኢይዝራኤል ወጡ። |
ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፤ ልትሸሽም ስትሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፌቡስቴ ነበረ።
ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።
አሁንም አንተ ከአንተም ጋር የመጡ የጌታህ ብላቴኖች ማልዳችሁ ተነሡ፤ ሲነጋም ተነሥታችሁ ወደ መጣችሁበት ሂዱ። ክፉ ነገርንም በልብህ አታኑር፤ በዐይኔ ፊት ጻድቅ ነህና፥ በነጋም ጊዜ ገሥግሣችሁ መንገዳችሁን ሂዱ” አለው። እነርሱም ሄዱ።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ሴቄላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በአዜብ በሰቄላቅም ላይ ዘምተው ነበር፤ ሴቄላቅንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፥