1 ሳሙኤል 28:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሳኦልና በብላቴኖቹም ፊት አቀረበችው፤ በልተውም ተነሡ፤ በዚያም ሌሊት ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ለሳኦልና ለሰዎቹ አቀረበችላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ በዚያም ሌሊት ተነሥተው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ለሳኦልና ለሰዎቹ አቀረበችላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ በዚያም ሌሊት ተነሥተው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምግቡንም ለሳኦልና ለባለሟሎቹ አቅርባላቸው ተመገቡ፤ በዚያኑም ምሽት ከዚያ ተነሥተው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሳኦልና በባሪያዎቹም ፊት አቀረበችው፥ በልተውም ተነሡ፥ በዚያም ሌሊት ሄዱ። |
ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።