የሶርያም ንጉሥ መንፈስ ስለዚህ እጅግ ተበሳጨች፤ አገልጋዮቹንም ጠርቶ፥ “ለእስራኤል ንጉሥ ማን እንደሚነግረው አትነግሩኝምን?” አላቸው።
1 ሳሙኤል 28:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጣች፤ እጅግም ደንግጦ እንደ ነበር አይታ፥ “እነሆ፥ እኔ አገልጋይህ ቃልህን ሰማሁ፤ ነፍሴንም በእጄ ጣልሁ፤ የነገርኸኝንም ቃል ሰማሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋ ወደ ሳኦል መጥታ እጅግ መደንገጡን ባየች ጊዜ እንዲህ አለችው፤ “እነሆ፤ አገልጋይህ ቃልህን ሰምቻለሁ፤ በነፍሴም ቈርጬ የነገርኸኝን ፈጽሜአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼ አለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼአለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጣች፥ እጅግም ደንግጦ እንደ ነበረ አይታ፦ እነሆ፥ እኔ ባሪያህ ቃልህን ሰማሁ፥ ነፍሴንም በእጄ ጣልሁ፥ የነገርኽኝንም ቃል ሰማሁ። |
የሶርያም ንጉሥ መንፈስ ስለዚህ እጅግ ተበሳጨች፤ አገልጋዮቹንም ጠርቶ፥ “ለእስራኤል ንጉሥ ማን እንደሚነግረው አትነግሩኝምን?” አላቸው።
የሚያድን እንደሌለም ባየሁ ጊዜ ሰውነቴን በእጄ አሳልፌ ለሞት በመስጠት ወደ አሞን ልጆች ተሻገርሁ፤ እግዚአብሔርም በፊቴ ጣላቸው፤ ለምንስ ዛሬ ልትወጉኝ ወደ እኔ መጣችሁ?” አላቸው።
ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊዉን ገደለ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ እስራኤልም ሁሉ አይተው ደስ አላቸው፤ በከንቱ ዳዊትን ትገድለው ዘንድ ስለምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ?”
ሳኦልም በዚያ ጊዜ በቁመቱ ሙሉ በምድር ላይ ወደቀ፤ ከሳሙኤልም ቃል የተነሣ እጅግ ፈራ። በዚያም ቀን ሁሉ፥ በዚያም ሌሊት ሁሉ እንጀራ አልበላምና ኀይል አልቀረለትም።
አሁን እንግዲህ አንተ ደግሞ የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ፤ በፊትህም ቁራሽ እንጀራ ላኑርልህ፤ መንገድም ትሄዳለህና ትበረታ ዘንድ ብላ” አለችው።