የዳዊትንም ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ከፍ ያደርግ ዘንድ መንግሥትን ከሳኦል ቤት ወሰዳት።”
1 ሳሙኤል 28:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በቃሌ እንደ ተናገረ አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለባልንጀራህ ለዳዊት ሰጥቶታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በእኔ የተናገረውን አድርጓል፤ እግዚአብሔር መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በእኔ የተናገረውን አድርጓል፤ ጌታ መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት የነገረህን ሁሉ እየፈጸመ ነው፤ መንግሥቱንም ከአንተ እጅ ወስዶ ለጐረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በቃሌ እንደ ተናገረ አድርጎአል፥ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል። |
የዳዊትንም ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ከፍ ያደርግ ዘንድ መንግሥትን ከሳኦል ቤት ወሰዳት።”
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ መጣ። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።
ጠላቱን ተቸግሮ አግኝቶ በመልካም መንገድ ሸኝቶ የሚሰድድ ማን ነው? ስለዚህ ለእኔ ስላደረግኸው ቸርነት እግዚአብሔር መልካሙን ይመልስልህ።