1 ሳሙኤል 25:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ደግሞ ከኢይዝራኤል አኪናሆምን ወሰደ፤ ሁለቱም ሚስቶቹ ሆኑለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ዳዊት ኢይዝራኤላዊቷን አኪናሆምን አገባ፣ ሁለቱም ሚስቶቹ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ዳዊት ኢይዝራኤላዊቷን አሒኖዓምን አግብቶ ነበር፥ ሁለቱም ሚስቶቹ ሆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ከዚህ በፊት የኢይዝራኤል ተወላጅ የሆነችውን አሒኖዓምን አግብቶ ነበር፤ አሁን ደግሞ አቢጌልን አገባ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ደግሞ ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ወሰደ፥ ሁለቱም ሚስቶች ሆኑለት። ሳኦል ግን የዳዊትን ሚስት ልጁን ሜልኮልን አገሩ ጋሊም ለነበረው ለሌሳ ልጅ ለፈልጢ ሰጥቶ ነበር። |
ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቤግያ ጋር ወደዚያ ወደ ኬብሮን ወጣ።
ለዳዊትም ወንዶች ልጆች በኬብሮን ተወለዱለት፤ በኵሩም ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበረ።
ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቤግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ።
ዳዊትና ሰዎቹም ማልደው ይሄዱ ዘንድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ሀገር ይመለሱ ዘንድ ተነሡ። ፍልስጥኤማውያንም ሊዋጉ ወደ ኢይዝራኤል ወጡ።
የዳዊትም ሁለቱ ሚስቶቹ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቤግያ ተማርከው ነበር።