እንዲህም ሆነ፤ አብራም ወደ ግብፅ ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤
1 ሳሙኤል 25:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውዬውም ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቤግያ ነበረ፤ ሴቲቱም ደግና ብልህ፥ መልክዋም እጅግ የተዋበ ነበረ፤ ሰውዬው ግን ጨካኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብሩም ክፉ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰውየው ስም ናባል፣ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢጌል ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውዮውም ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ፥ የሴቲቱም አእምሮ ታላቅ፥ መልክዋም የተዋበ ነበረ፥ ሰውዮው ግን ባለጌ ነበረ፥ ግብሩም ክፉ ነበረ፥ ከካሌብም ወገን ነበረ። |
እንዲህም ሆነ፤ አብራም ወደ ግብፅ ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤
በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ድርሻውን ሰጠው፤ ኢያሱም የዔናቅ ዋና ከተማ የሆነችውን የአርቦቅን ከተማ ሰጠው። እርስዋም ኬብሮን ናት።
ስለዚህም በጌታችንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እንዲመጣ ተቈርጦአልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊናገረው አይችልምና የምታደርጊውን ተመልከቺና ዕወቂ።”
በዚህ ክፉ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጥል እለምናለሁ፤ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስንፍናም አድሮበታል፤ እኔ ባሪያህ ግን አንተ የላክሃቸውን ብላቴኖችህን አላየሁም።
እኛም በከሊታውያን አዜብ፥ በይሁዳም በኩል፥ በካሌብም አዜብ ላይ ዘመትን፥ ሴቄላቅንም በእሳት አቃጠልናት” አለው።