La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 25:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚህ ክፉ ሰው በና​ባል ላይ ጌታዬ ልቡን እን​ዳ​ይ​ጥል እለ​ም​ና​ለሁ፤ እንደ ስሙ እን​ዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስን​ፍ​ናም አድ​ሮ​በ​ታል፤ እኔ ባሪ​ያህ ግን አንተ የላ​ክ​ሃ​ቸ​ውን ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን አላ​የ​ሁም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጌታዬ፣ ያን ምናምንቴ ሰው ናባልን ከቁም ነገር አይቍጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለ ሆነ፣ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም ዐብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጕልማሶች አላየኋቸውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታዬ፥ ያን ባለጌ ሰው ናባልን ከቁምነገር አይቁጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለሆነ፥ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም አብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጐልማሶች አላየኋቸውም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የናባልን ጉዳይ ከቁም ነገር አታግባው! እርሱ ልክ እንድ አስሙ አጠራር ሞኝ ነው! ጌታዬ፥ የአንተ አገልጋዮች በመጡ ጊዜ እኔ በዚያ አልነበርኩም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚህ ምናምንቴ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጣል እለምናለሁ፥ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፥ ስሙ ናባል ነው፥ ስንፍናም አድሮበታል፥ እኔ ባሪያህ ግን ከአንተ የተላኩትን የጌታዬን ጕልማሶች አላየሁም።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 25:25
9 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም የሞተ አም​ኖን ብቻ ነው እንጂ የን​ጉሥ ልጆች ሁሉ ሞቱ ብሎ ጌታዬ ንጉሡ ይህን ነገር በልቡ አያ​ስብ።”


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሰነ​ፍን አለቃ ይሆን ዘንድ ግድ አይ​ሉ​ትም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ሎሌህ ዝም በል አይ​ል​ህም።


ስለ​ዚህ የቍ​ጣ​ውን መዓ​ትና የሰ​ል​ፉን ጽናት አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸው አቃ​ጠ​ላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁም፤ በል​ባ​ቸ​ውም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።


ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድዳባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፣ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።


ስለ​ዚ​ህም በጌ​ታ​ች​ንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እን​ዲ​መጣ ተቈ​ር​ጦ​አ​ልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊና​ገ​ረው አይ​ች​ል​ምና የም​ታ​ደ​ር​ጊ​ውን ተመ​ል​ከ​ቺና ዕወቂ።”


በእ​ግ​ሩም ላይ ወደ​ቀች፤ እን​ዲ​ህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢ​ኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪ​ያህ በጆ​ሮህ ልና​ገር፥ የባ​ሪ​ያ​ህ​ንም ቃል አድ​ምጥ።


አሁ​ንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ት​ገ​ባና፥ እጅ​ህን እን​ድ​ታ​ድን የከ​ለ​ከ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ች​ህና በጌ​ታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።


የሰ​ው​ዬ​ውም ስም ናባል፥ የሚ​ስ​ቱም ስም አቤ​ግያ ነበረ፤ ሴቲ​ቱም ደግና ብልህ፥ መል​ክ​ዋም እጅግ የተ​ዋበ ነበረ፤ ሰው​ዬው ግን ጨካ​ኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብ​ሩም ክፉ ነበረ።