አህያውንም አስጭና ሎሌዋን፥ “ንዳ፥ ሂድ፤ እኔ ሳላዝዝህ አታዘግየኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ቄርሜሎስ ተራራ እንሂድ” አለችው።
1 ሳሙኤል 25:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም በአህያዋ ላይ ተቀምጣ በተራራው ላይ በተሰወረ ስፍራ በወረደች ጊዜ፥ እነሆ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እርስዋ ወርደው ተቀበሏት፤ እርስዋም ተገናኘቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በአህያዋ ላይ ተቀምጣ ወደ ሸለቆው በምትወርድበት ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እርሷ ወረዱ፤ እርሷም አገኘቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም በአህያዋ ላይ ተቀምጣ ወደ ሸለቆው በምትወርድበት ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እርሷ ወረዱ፤ እርሷም አገኘቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም በአህያ ላይ ተቀምጣ እየጋለበች በኮረብታው ጥግ በሚገኘው ጠመዝማዛ መንገድ ስትወርድ በድንገት ዳዊትና ተከታዮቹ ወደ እርስዋ ሲመጡ አገኘቻቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በአህያዋ ላይ ተቀምጣ በተራራው ላይ በተሰወረ ስፍራ በወረደች ጊዜ፥ እነሆ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እርስዋ ወረዱ፥ እርስዋም ተገናኘቻቸው። |
አህያውንም አስጭና ሎሌዋን፥ “ንዳ፥ ሂድ፤ እኔ ሳላዝዝህ አታዘግየኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ቄርሜሎስ ተራራ እንሂድ” አለችው።
ለአገልጋዮችዋም፥ “አስቀድማችሁ በፊቴ ሂዱ፤ እነሆም እከተላችኋለሁ” አለች። ይህንም ለባልዋ ለናባል አልነገረችውም።
ዳዊትም አለ፥ “ለዚህ ሰው ከሆነው ሁሉ አንድ ነገር እንዳይጠፋበት በእውነት ከብቱን ሁሉ በምድረ በዳ በከንቱ ጠበቅሁ፤ ከገንዘቡ ሁሉ አንዳች ይወስዱበት ዘንድ ያዘዝነው የለም፤ እርሱም በበጎ ፋንታ ክፉ መለሰልኝ።