La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 25:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ዋም፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ በፊቴ ሂዱ፤ እነ​ሆም እከ​ተ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አለች። ይህ​ንም ለባ​ልዋ ለና​ባል አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም አገልጋዮቿን፣ “ቀድማችሁኝ ሂዱ፤ እኔም እከተላችኋለሁ” አለቻቸው፤ ለባሏ ለናባል ግን አልነገረችውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም አገልጋዮቹን፥ “ቀድማችሁኝ ሂዱ፤ እኔም እከተላችኋለሁ” አለቻቸው፤ ለባሏ ለናባል ግን አልነገረችውም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም በኋላ አገልጋዮቹን “ቀድማችሁኝ ሂዱ፤ እኔም እከተላችኋላሁ” አለቻቸው፤ ለባልዋ ግን የነገረችው ቃል አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለብላቴኖችዋም፦ አስቀድማችሁ በፊቴ ሂዱ፥ እነሆም፥ እከተላችኋለሁ አለች። ይህንም ለባልዋ ለናባል አልነገረችውም።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 25:19
9 Referencias Cruzadas  

መን​ጎ​ቹ​ንም ለየ​ብቻ ከፍሎ ለብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሰጣ​ቸው፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም፥ “በፊቴ እለፉ፤ መን​ጋ​ውን ከመ​ን​ጋው አርቁ” አላ​ቸው።


እን​ዲ​ሁም ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንና ሦስ​ተ​ኛ​ውን፥ በፊቱ የሚ​ሄ​ዱ​ት​ንና መን​ጋ​ውን የሚ​ነ​ዱ​ትን ሁሉ እን​ዲሁ ብሎ አዘዘ፦“ ወን​ድሜ ዔሳ​ውን ባገ​ኛ​ች​ሁት ጊዜ ይህ​ንኑ ነገር ንገ​ሩት፤


እን​ዲ​ህም በሉ፦ እነሆ አገ​ል​ጋ​ይህ ያዕ​ቆብ ከኋ​ላ​ችን ነው። በፊቴ በሚ​ሄ​ደው እጅ መንሻ እታ​ረ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ምና​ል​ባት ይራ​ራ​ል​ኛል፤ ፊቱ​ንም አያ​ለሁ ብሎ​አ​ልና።”


እጅ መን​ሻ​ውን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ላከ፤ እርሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሰ​ፈር አደረ።


በነ​ጋም ጊዜ፥ የሳ​ኦል ልጅ ዮና​ታን ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “ና፤ በዚያ በኩል ወዳ​ለው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር እን​ለፍ” አለው፤ ለአ​ባ​ቱም አል​ነ​ገ​ረ​ውም።


እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ተቀ​ምጣ በተ​ራ​ራው ላይ በተ​ሰ​ወረ ስፍራ በወ​ረ​ደች ጊዜ፥ እነሆ፥ ዳዊ​ትና ሰዎቹ ወደ እር​ስዋ ወር​ደው ተቀ​በ​ሏት፤ እር​ስ​ዋም ተገ​ና​ኘ​ቻ​ቸው።


አቤ​ግ​ያም ወደ ናባል መጣች፤ እነ​ሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደ​ርግ ነበር፤ ናባ​ልም እጅግ ሰክሮ ነበ​ርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም ነበር።