1 ሳሙኤል 25:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንጀራዬንና የወይን ጠጄን፥ ለሸላቾቼም ያረድሁትን ሥጋ ወስጄ ከወዴት እንደ ሆኑ ለማላውቃቸው ሰዎች እሰጣለሁን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ እንጀራዬንና ውሃዬን እንዲሁም በጎቼን ለሚሸልቱልኝ ሰዎች ያረድሁትን ፍሪዳ ከየት እንደ መጡ ለማይታወቁ ሰዎች የምሰጠውስ ለምንድን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ እንጀራዬንና ውሃዬን እንዲሁም በጎቼን ለሚሸልቱልኝ ሰዎች ያረድሁትን ፍሪዳ ከየት እንደመጡ ለማይታወቁ ሰዎች የምሰጠውስ ለምንድን ነው?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እንጀራዬንና ውሃዬን እንዲሁም ለበጎች ሸላቾቼ ያረድኳቸውን እንስሶች አንሥቼ ከወዴት እንደ መጡ ለማላውቃቸው ሰዎች የምሰጥበት ምክንያት የለም!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጀራዬንና የወይን ጠጄን ለሸላቾቼም ያረድሁትን ሥጋ ወስጄ ከወዴት እንደ ሆኑ ለማላውቃቸው ሰዎች እሰጣለሁን? ብሎ መለሰላቸው። |
እንደማይታወቁ ስንታይ የታወቅን ነን፤ እንደ ሰነፎች ስንታይም ልባሞች ነን፤ እንደ ሙታን ስንታይ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆንም አንገደልም።
ጌዴዎንም ወደ ሱኮት አለቆች መጥቶ፥ “ለደከሙት ሰዎችህ እህል እንሰጥ ዘንድ የዛብሄልና የስልማና እጅ አሁን በእጅህ ነውን? ብላችሁ የተላገዳችሁብኝ፥ ዛብሄልና ስልማና እነሆ፥” አለ።
እግዚእብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤ እግዚአብሔርም አንተን ይበቀልልኝ፤ እጄ ግን በአንተ ላይ አትሆንም።
የሰውዬውም ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቤግያ ነበረ፤ ሴቲቱም ደግና ብልህ፥ መልክዋም እጅግ የተዋበ ነበረ፤ ሰውዬው ግን ጨካኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብሩም ክፉ ነበረ።
አሁንም በጎችህ እንደሚሸለቱ ከእኛ ጋር በምድረ በዳ ያሉ ሰዎች ነገሩን፤ እኛም አልከለከልናቸውም፤ በቀርሜሎስም በነበሩበት ዘመን ሁሉ ከመንጋቸው ይሰጡን ዘንድ አላዘዝናቸውም።