በውስጥሽ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ሌቦች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ፤ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፤ በመካከልሽም የማይገባ ነገርን አደረጉ።
1 ሳሙኤል 24:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከዚያ መጥቶ በዓይን ጋዲ በጠባብ ቦታ ተቀመጠ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ከተመለሰ በኋላ፣ “እነሆ፤ ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ከዚያ ወደ ላይ ወጥቶ በዔንገዲ ምሽጎች ተቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ወግቶ ከተመለሰ በኋላ ዳዊት በዔንገዲ አጠገብ በሚገኘው ምድረ በዳ የሚገኝ መሆኑን ሰማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ከተመለሰ በኋላ፦ እነሆ፥ ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ አለ የሚል ወሬ ደረሰለት። |
በውስጥሽ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ሌቦች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ፤ በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ በሉ፤ በመካከልሽም የማይገባ ነገርን አደረጉ።
ዓሣ አጥማጆችም ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ በዚያ ይቆማሉ። ያም መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።
የዚፍ ሰዎችም ከአውክሞዲስ ወደ ሳኦል ወደ ኮረብታው ወጥተው እንዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ቀኝ በጠባቡ በኩል በኤኬላ ኮረብታ ላይ በቄኒ ውስጥ በማሴሬት በእኛ ዘንድ ተሸሽጎ የለምን?