1 ሳሙኤል 23:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ በዚህ በይሁዳ መቀመጥ እንፈራለን፤ ይልቁንስ ፍልስጥኤማውያንን ለመዝረፍ ወደ ቂአላ ብንሄድ እንዴት እንሆናለን?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት ሰዎች ግን፣ “እዚሁ በይሁዳ ምድር እያለን እየፈራን ነው፤ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ለመውጋት ወደ ቅዒላ የምንሄድ ከሆነማ ምን ያህል የሚያስፈራ ነው?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት ሰዎች ግን፥ “እዚሁ በይሁዳ ምድር እያለን እየፈራን ነው፤ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ለመውጋት ወደ ቅዒላ የምንሄድ ከሆነማ ምን ያህል የሚያስፈራ ነው?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የዳዊት ተከታዮች “በዚህ በይሁዳ ስንኖር የምንፈራው ብዙ ነገር አለ፤ አሁን ደግሞ ወደ ቀዒላ ሄደን በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ላይ አደጋ ብንጥል ችግራችን የባሰ ችግር ይገጥመናል!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ሰዎች፦ እነሆ፥ በዚህ በይሁዳ መቀመጥ እንፈራለን፥ ይልቁንስ በፍልስጥኤማውያን ጭፍሮች ላይ ወደ ቅዒላ ብንሄድ እንዴት ነው? አሉት። |
እግሮችህ ሮጠው ይደክማሉ፤ ፈረሶችን ለምን ታስጌጣለህ? በሰላምም ምድር ላይ ለምን ትታመናለህ? በዮርዳኖስስ ጩኸት ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?
ዳዊትም፥ “ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያንን ልምታን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቂአላንም አድን” አለው።
እንግዲህ ዕወቁ፤ ከአያችሁ በኋላ ከእናንተ ጋር እንሄዳለን፤ በዚያችም ምድር ካለ በይሁዳ አእላፍ ሁሉ እፈትሻታለሁ።”
ሳኦልና ሰዎቹም በተራራው በአንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በሌላው ወገን ሄዱ። ዳዊትም ከሳኦል ፊት ያመልጥ ዘንድ ተሰውሮ ነበር። ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ከብበዋቸው ነበርና።
ዳዊትም ደግሞ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም መልሶ፥ “ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁና ተነሥተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው።