ብላቴኖቹም ሁሉ ተከተሉት፤ ኬልቲያውያንና ፌልታውያንም ሁሉ በምድረ በዳ በወይራ ሥር ቆሙ። ሕዝቡም ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎችም ሁሉ ስድስት መቶ ነበሩ። ከእርሱ ጋር ፌልታውያንና ኬልቲያውያን፥ በእግራቸው ከጌት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያንም ነበሩ። በንጉሡም ፊት ይሄዱ ነበር።
1 ሳሙኤል 23:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎችም ተነሥተው ከቂአላ ወጡ፤ ወደሚሄድበትም ይከተሉት ነበር። ሳኦልም ዳዊት ከቂአላ እንደ ሸሸ ሰማ፤ ስለዚህም ከመውጣት ቀረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎቹ ከቅዒላ ተነሥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ፤ ዳዊት ከቅዒላ መሸሹን በሰማ ጊዜ፣ ሳኦል ወደዚያ መሄዱን ተወ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎቹ ከቅዒላ ተነሥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ፤ ዳዊት ከቅዒላ መሸሹን በሰማ ጊዜ፥ ሳኦል ወደዚያ መሄዱን ተወ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ተከታዮቹ በሙሉ ወዲያውኑ ቀዒላን ለቀው ለመሄድ ተንቀሳቀሱ፤ ሳኦልም ዳዊት ከቀዒላ አምልጦ መሄዱን በሰማ ጊዜ የነበረውን ዕቅድ ተወ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎችም ተነሥተው ከቅዒላ ወጡ፥ መሄድም ወደሚችሉበት ሄዱ። ሳኦልም ዳዊት ከቅዒላ እንደ ሸሸ ሰማ፥ ስለዚህም ከመውጣት ቀረ። |
ብላቴኖቹም ሁሉ ተከተሉት፤ ኬልቲያውያንና ፌልታውያንም ሁሉ በምድረ በዳ በወይራ ሥር ቆሙ። ሕዝቡም ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎችም ሁሉ ስድስት መቶ ነበሩ። ከእርሱ ጋር ፌልታውያንና ኬልቲያውያን፥ በእግራቸው ከጌት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያንም ነበሩ። በንጉሡም ፊት ይሄዱ ነበር።
የመጣኸው ትናንት ነው፤ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙርህን? እኔ ወደምሄድበት እሄዳለሁ፤ አንተ ግን ተመለስ፤ ወንድሞችህንም ከአንተ ጋር መልሳቸው፤ እግዚአብሔርም ምሕረቱንና እውነቱን ያድርግልህ” አለው።
የተጨነቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለበት ሁሉ፥ የተከፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰባሰበ፤ እርሱም በላያቸው አለቃ ሆነ፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ።
ዳዊትም ሰዎቹን፥ “ሁላችሁ ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም ሰይፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎችም ዳዊትን ተከትለው ወጡ፤ ሁለት መቶውም በጓዛቸው ዘንድ ተቀመጡ።