1 ሳሙኤል 20:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም መሣሪያውን ለብላቴናው ሰጥቶ፥ “ሂድ ወደ ከተማ ግባ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዮናታን የጦር መሣሪያውን ለልጁ ሰጥቶ፣ “ይዘህ ወደ ከተማ ተመለስ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዮናታን የጦር መሣሪያውን ለልጁ ሰጥቶ፥ “ይዘህ ወደ ከተማ ተመለስ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታንም ያንን ልጅ “መሣሪያዎቼን ይዘህ ወደ ከተማ ተመለስ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም መሣርያውን ለብላቴናው ሰጥቶ፦ ወደ ከተማ ውሰድ አለው። |
ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤርገብ ተነሣ፤ በምድርም ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእርሳቸውም ተሳሳሙ፤ ለረዥም ሰዓትም ተላቀሱ።