እንዲህም ሆነ በነጋው ዮናታን ከዳዊት ጋር ምልክት ለማድረግ ወደ ተቃጠረበት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእርሱም ጋር ታናሽ ብላቴና ነበረ።
1 ሳሙኤል 20:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናውንም፥ “ሮጠህ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልግልኝ” አለው። ብላቴናውም በሮጠ ጊዜ ዮናታን ፍላጻውን ወደ ማዶ አሳልፎ ወረወረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁንም፣ “ሩጥ! የምሰዳቸውን ፍላጻዎች ፈልጋቸው” አለው፤ ልጁም በሮጠ ጊዜ፣ ከርሱ አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጁንም፥ “ሩጥ! የምሰዳቸውን ፍላጻዎች ፈልጋቸው” አለው፤ ልጁም በሮጠ ጊዜ፥ ከእርሱ አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁንም “ፈጥነህ ሂድና የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልገህ አምጣልኝ” አለው፤ ልጁም ሲሮጥ ዮናታን ከዚያ ልጅ ፊት አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናውንም፦ ሮጠህ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልግልኝ አለው። ብላቴናውም በሮጠ ጊዜ ፍላጻውን ወደ ማዶ ወረወረው። |
እንዲህም ሆነ በነጋው ዮናታን ከዳዊት ጋር ምልክት ለማድረግ ወደ ተቃጠረበት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእርሱም ጋር ታናሽ ብላቴና ነበረ።